ሳምንት 48 ፊደል እና ልሳን

የዛሬው ፊደል እና ልሳን ለጉብል እና ለሆደ ቡቡ አይሆንም፡፡የዚህ ሳምንት መሰናዶ አማረኛ ሰለለ ተበተ እያለ ለሚከፋ ሰው የሚሆን ነገር የለውም፡፡መስመር ልናልፍ እንችላለን፣ክልክል ልንጥስ እንችላለን፣ገደብ ልናፈርስ እንችላለን፡፡እና ከለመድከው ክበብ አንገትህን ብቅ ባደረክ ቁጥር አንዳች ነገር ንዴት ውልብ ሚልብህ ከሆንክ ከኛ ለጥቆ ሁነኛ የነጠላ ዜማዎች ቻናል አለ እዚያ ቆይ፡፡ለዛሬ እኛ አንሆንህም፡፡

ከተመስገን ደሳለኝ ጋር ምሳ እንበላለን-ወደህ ግባበት፤የአሳዬ ደርቤን ዱላ እና የሙሴን በትር እናወዳድራለን-መብታችን ነው፤ከውብሸት ታደለ ጋር ቁጭ ብለን አንድ ሊስትሮ አስቁመን ‹‹ ህዝብ ጠላትህ ነው›› እያልን ልቡን እናሻክረዋለ-እንግዲህ ምንትሆን፡፡አንድ ትርጉም ወግ አናጣልህም-እሱ እንኳ የሚያስከፋህ አይመስለኝም፡፡አዳዲስ መጽፍትን እንጋብዝሃለን ደግሞ፡፡

ለማንኛውም የዛሬው ድንኳን መግቢያ ይሄውልህ፡፡የፈራ ካለ ይሄኔ ይመለስ፡፡

ሸግዬ ሳምንት ይሁንላችሁ፡፡

Watch more Ethiopian videos daily at abbaymedia.info Also, like us on facebook @ abbaymedia.info and follow us on twitter @ abbaymedia.info

11 COMMENTS

  1. የሊስትሮው ኑሮ የአብዛኛው ኢትዮጵያዊ አኗኗር ነው ።ከሰልና ማንደጃ ተጠቃሚ ቀንሷን ምክንያቱም የኤሌትሪክ ማንደጃ ተጠቃሚው ስለበረከተ …የልብስ አጣቢዎችና የሳፋ ተፈላጊነት ቀንሷል ምክንያቱም ዜጎቻችን ዘምነው አውቶማቲክ የልብስ ማጠቢያ ማሽን ይጠቀማሉ… ጥሩ አየር ለማግኘት እንደ ድሮው ዛፍ የሚተክል ሰው የለም ምክንያቱም ቬንትሌተር ተጠቃሚው ከቀን ቀን ጨምሮአል ሌላው ቀርቶ ዶሮ ሲጮህ ከእንቅልፍ መነሳት ቀርቶ ተጋድሞ እየዋሉ አላርም ሆኗል ቀስቃሹ ….ወገን ዘመን ዘመነኞቹን ወዴት እየመራች ነው ???

Comments are closed.