51 COMMENTS

 1. እኛ እኮ ለጉድ የበቀልን ነን!!

  ዘንድሮ ሁሉ ነገር ባቢሎን ሆኖብኛል ። በቃ ምንም ነገር አውርተን መግባባት እኮ አልቻልንም!!! በቃ ምንም ነገር!!! ለምሳሌ አንድ ፅሁፍ ፖስት ቢደረገ የሆነ ሰው ጋር ሲደርስ የሚኖረው ትርጉም አንዳንዴ ፖሳቹ እንኳን ሊያስበው ቀርቶ በጭራሽ ሊገምተው እንኳን በማይችለው መልኩ ተተርጉሞ ከስር ሰዎች በኮመንት ሲጨፋጨፉ ታያላችሁ።
  ለምሳሌ እኔ እንዲ ብዪ ፖስት ባደርግ ምሳሌ ነው አሉ እንግዲህ

  የኔ ፖስት ፤ . . . ""ለሰው ሞት አነሰው"" !!

  <<<ኮመንት ሊጀመር ነው እንግዲህ>>>

  ‘ሀዊ’፤… በትክክል ተስፍሽ ልክ ነህ ለሰው ሞት ሲያንሰው ነው

  ‘ቲቲ’ ፤…ምን ለማለት ፈልገህ ነው? ተስፍሽ የሚሉህ . . . . አንቺ ሀዊ ደግሞ አታሽቃብጪ

  ‘ዴቭ’፤ …አቦ የሽማግሌ ተረትህን እዛው አይነፋም ሼባ ነግር ነህ

  ‘አስቴር’፤ …እግዚያብሄር ይባርክህ ልክ ነው ግን አይዞህ ምን ሆነህ ነው? እመቤቴ ትረዳሀለች አይዞህ ፀልይ

  ‘ዲና’፤ …ማነሽ አስቴር የሚሉሽ ዝም ብለሽ አታውሪ እየሱስ ጌታ ነው ጌታ ያውቃል ነው የሚባለው

  ‘ዘለቀ’፤ . . . የሆንሽ ክፍታፍ ነሽ እኛ እየሱስ ዘበኛ ነው አልን? አንቺ ዲና የሚሉሽ ደደብ

  "አስካሉ ለማ"፤ . . . ስማ ዘለቀ ሰው ደደብ እና ደንቆሮ አይባልም እ/ር ይቅር ይበልህ !!! ደንቆሮ ብሎ መሳደብ ትልቅ ሀጥያት ነው በጣም ትልቅ አይባልም ። አንተ ግ ን ደደብ ደንቆሮ ነህ እሺ!

  ‘ሚጣ ያባቷ’፤ …እስቲ ዘፈን ጋብዙኝ በናታችሁ ደብሮኛል እኔ ምን አገባኝ ለሰው ሞት ምናምን የምትሉኝ

  ‘መቅዲ ላቭ’፤ …ጉድ ያረገኝ ፍቅርሽ ነው የቴዶን ስሚው እኔ እሱን እየሰማሁ ነው

  ‘መአዛ’፤ . . . አንቺ ሚጡ የሚሉሽ ባለጌ እና መቅዲ የሚሉሽ ሞዛዛ በፍልሰታ ነው ዘፈን የምትሰሚው ይድፋቹ

  ‘መሪማ ሀሰን’፤ …ሱባን አላህ እረ በአላህ እንዲ አትሰዳደቡ በቃ እሱ ያለው ለሰው ሞት አነሰው ነው እኮ

  ‘ማቲዎስ፤ …አንቺ’ ጥፍጥፍ መሪማ ምን ትሰሪያለሽ እዚህ እዛው ሳህንሽን እጠቢ ዝፍጥ

  ‘ሀጎስ በርሄ’፤… ልክ ነህ ለሰው ሞት ሲያንሰው ነው ሀገራችን እዚህ የደረሰችው ለሰው ሞት አንሶት ነው።

  ‘አባይ ደምለው’፤ …ስማ አንተ ሀጎስ ወያኔ ሌባ የቀን ጅብ ምን ትሰራልህ እዚህ ላንተ ነው ሞት ሲያንስ የተባለው።

  "አብረህት " ; . . . ዋ! አታ ዝም ቦል አወይ አሁን አሸንዳ ነው ለምን ስለ አሸንዳ አታወራም እንኳን አደረሰህ

  ‘ሊሊ ማር’፤ …እንኳን አብሮ አደረሰን የሰላም ያድርግልን አሜን።

  ‘ናቲ ማን’፤ …በለው አንቺ ሊሊ ምናምን የሚሉሽ ቆይ ማን እንኳን አደረሰሽ አለሽ? መጀመሪያ አንብቢ ዶማ።

  ‘ሄኒ ዘ ማን’፤ . . . ሊሊዬ በውስጥ መስመር አውሪኝ

  "ሁሴን" : . . . ፍትህ ለአክሱም ሙስሊሞች ቆይ ግ ን ተስፍሽ መቼ ነው ስለ አክሱም የምትጮህው?

  "ሳባ" ፤ . . . ሁሴን አርፈህ አትቀመጥም? ምን ይመስላል?

  "ወልዱ". . . . እረ ልክ ነህ ለሰው ሞት አነሰው ተስፍሽ ፍትህ ለኢንጂነር ስመኘው!

  ‘አበጀ ለማ’፤ …እንግዲህ ወንድሜ ያው ለሰው ሞት አነሰው ለማለት ያነሳሳህ የራስህ ጉዳይ ስለሚኖርህ እኔ ለምን አልልህም ግን ቆይ ማን እንዲ ቢያንገበግብህ ነው እንዲ የሆንከው? ለማን ብለህ ነው ደግሞ አይዞሕ።

  ‘ጄሪ’፤ …ወይኔ አበጀ የድሮ አማርኛ አስተምሪ ነህ እንዴ? ምንድነው መንበዛበዝ?

  እያለ እያለ ይቀጥላል ምንም ማለቂያ የለውም በቃ በዚህ ደረጃ እዚህ ደርሰንላችኋል እኔ እማ አንዳንድ ግዜ ከባቢሎንም በላይ የሆነ የማላውቀው ፕላኔት ላይ ሁሉ ያለው እኮ ነው የሚመስለኝ።
  ብዬ ብደመድመው እንኳን በመጨረሻም

  ሌላ ኮመንት
  ‘ማርታ’፤ …ባቢሎምን ግን ምንድነው?

  ‘ሳምሶን’፤ ባቢሎን በሳሎን የሚል ድራማ ነው

  "ታየች "፤… ኮሜንት ላነብ ነው የገባሁት!!

  ‘ገለታ’፤ ማንን ለመንካት ነው ባቢሎን ያልከው ኦሮሚያ መቼም እስከመቼም አትቀየርም

  እያለ ይቀጥላል ማለቂያ የለውም እኔ እዚጋር ባቆም ይሻለኛል እናንተ ቀጥሉጥ
  ተስፍሽ ነኝ ከ TST APP

LEAVE A REPLY