4 COMMENTS

 1. Ethiopia's claim of being the only country in Africa to never be colonized came at the expense of Eritrea's sovereignty and independence.

  In 1889, the Italians signed the Treaty of Wuchale with then Ethiopian king Menelik II who essentially granted Eritrea to Italy in exchange for recognition of Ethiopian sovereignty. Italy also promised Menelik II financial assistance and military supplies.

  Eventually, Ethiopia did defeat Italy in the battle of Adwa (approx. 100,000 Ethiopians vs 20,000 Italians) and afterwards Menelik signed an agreement recognizing Eritrea as a sovereign state of Italy. Basically, Eritrea was used as a political tool to gain leverage with the Italian colonialist when it was convenient for Ethiopia's survival.

  This should explain the Derg's barbaric regime, Woyane's betrayal and the common attitude of entitlement towards Eritrea.

 2. ኢትዮጵያዊነት እንጅ።
  ።።።።።።።።።።።።።።
  አብዲሳ አብርሀም፣ደቦጭ ወንድሙና አጋሮቹ
  ለፋሽስት ከፋፍለህ ግዛው በእጅጉ ያልተመቹ
  ዘራይ እሮም ላይ የሳት ነበልባል ሲተፋ
  ቴወድሮስ መቅደላ አምባ ላይ እራሱን በክብር ሲያጠፋ
  እስላም ክርስቲያን ዜጎቿ ስለ ኢትዮጵያ ክብር የማሉ
  ዮሃንስ እምየ አሉላ ወራሪን ህልሙን ሲያቀሉ
  በላይ አቤቾ አርበኞች እምቢ አሻፈረኝ እያሉ
  እልፍ አልአፍ ሰማዕታት ለእምየ ክብር የተቀሉ
  በንፁህ ኢትዮጵያዊን ሞት የሀገሬ ጋራ ሸንተረሮሮቿ ወንዞቿ በደም ሲቀሉ
  ሳዲቁ አቡነ ጴጥሮስ ህዝቤን ባሪያ ሁን ብየ አልግዝትልህም ሲሉ
  የባንዲራ ነገር ሲነሳ መቸ እምነት ብሄር ቋንቋ አሉ
  ኃይሌ አበበ ምሩፅ በላይነህ ለሀገሬ የወርቅ ሜዳሊያ ክብር እና ሞገስ ሲያድሉ
  መሰረት ጥሩነሽ ደራርቱ አልማዝ እጅጋየሁ ገንዘቤ እሩጠው ቀድመው ሲገቡ
  ከድር ስለሽ ሌሊሳ
  ብርሀኑ ከበደ ቀናኒሳ
  ሀጎስ መዝገቡ ካጅልሳ
  ሌሎች ዕንቁዎቻችን ጉሮ ወሸባየ ሲያስብሉ
  ከሚውለበለው ባንዲራ ጀርባ ኢትዮጵያዊነትን እንጅ እንደ ከፋፋዮቻችን መች የብሄር ስሌት ቢያሴሉ
  ***********************
  እምየ ሚኒሊክ
  ።።።።።።።።።።
  ከጎጠኞች የማይገጥመው ስለ አፄ ሚኒሊክ ያለኝ ለየት ያለው እይታየ።

  በዘመኑ በምንም አይነት የጦር ሜዳ ትጥቅ መመዘኛ ከማይስተካከሉት እሰከ አፍንጫው ከእብሪት እና የመርዝ ጭስ ጋር በከባድ መሳሪያና አውሮፕላን የተደገፈ እግረኛ የፋሽስት ኢጣሊያን ጦርን በትንሽ ጊዚያት ውስጥ ድባቅ የመቱት የኢትዮጵያ አርበኞች
  አፄ ሚኒሊክ
  ብሄራዊ ውትድርና ጠርተው
  ህፃናትን ከእናት ጉያ ነጥቀው
  የበቀል ጠበንጃ አሸክመው
  ወይም አገሬውን አስገድደው አይደለም።
  በአንፃሩ እንደስማቸው
  እውነትም እንደመየነታቸው
  ሩህሩህነታቸው
  ፍርድ አዋቂነታቸው
  ፍርሃተ እግዜሄርነታቸው
  ሁሉንም በአንድ ኢትዮጵያ የዓይን ብሌን በማየታቸው
  ጉልበት ያለህ በጉልበትህ
  ስንቅ ያለህ በስንቅህ
  ተወራለችና በሶላቶ ፋሽስት ኢትዮጵያ ሀገርህ
  በግፍ በወደቁት ሰማዕታት ስም ይዠሃለሁ
  የኢትዮጵያ አይደለም ህዝቧ ምድሯም ታወግዝሃለች
  ጨርቄን ማቄን ሳትል ጋሻና ጦርህን ይዘህ ተከተለኝ አሉት።

  እምየ እንኳን ለምነው ጠርተውት
  ግዳጅ ነው ቢሉት
  ማያሳፍራቸው ወገናቸው
  ለተመኙት ድል አበቃቸው።
  ይህም ገድላቸው
  አይደለም እምየ ለሚላቸው
  የኢትዮጵያ ህዝብ በቅኝ ግዛት ስር ወድቀው ለነበሩት አገራትም ትልቅ የነፃነት ተስፋን አበሰረ።

  ለእጣልያንና ሀያል ነን ለሚሉት ሀገሮች ዳግም የሀፍረት ሸማ አከናነበ። በዶጋሌው ሽንፈት ቂምን ቋጥሮ ለመጣው የኢጣሊያን ጦር ዳግም አሉላን ከማስተወስ አልፎ የእሳቸውንም ድል አድራጊነት ሲያስታውሰው
  ሚኒሊክ እጅግ ሀዘን በሰበረው መንፈስ ወደሗላ ነጉደው
  በሁለቱ ቀደምት አፄዎችና አሁንም በህዝባቸው ላይ ፋሽስት በግፍ ባደረሰው ግድያ ተክዘው ከተመሰጡበት ሃሳብ ሲነቁ ፊት ለፊታቸው ከሚውለበለበው ባንዲራ ላይ እንደገና አይናቸውን ተክለው እንባ በሚተናነቀው ምዕናባቸው ይስሏቸው ጀመር።

  እንዲህም አሉ። ህያው ገድላችሁ ሁሌም በየሰንደቁ በባንዲራው ላይ ይታያል።
  የቀረውም አለም ከአቢሲያኖች ጋር አትተናኩል ለወደዳቸው ማር ለጠላቸው እሬት ናቸውና ሲል ይደመጥ ጀመር። አዝማሪም ይህን አስተርጉሞ ያቀነቅነው ጀመር
  ከአላመንከኝ
  የጉንዲጉንዲ የአምባለጌ የዶጋሌ የውጫሌ የመተማ የመቅደላ የአድዋ የፍቸ ወዘተርፈ የመሀል ሀገር በአራቱም ማዕዘን
  ሜዳ እና ሽንተረሯን
  ጠይቃቸው የኢትዮጵያን።
  ታዲያ የነዚህ ሀውልት አልባ ሰማዕታት መልሳቸውም
  ለወደፊት እዚህ ድረስ እንዳትደክም
  በጀግኖቹ ሰማዕታት ክቡር አጥንትና ደም
  ታሪክህ ተፅፎልሃል በአረንጓዴ ቢጫ ቀይ ቀለም
  ብለው ያስተክዙሃል ዳግም
  ሊወራት ሚመኛትም ሳይወድ በግድ እንዲህ ሲል ስንኝ ቋጥሯል።

  Don't mess with the Abyssinians
  They are dignified righteous
  down to earth Humble nations
  On the battle field true warrior wild bees
  Go some where else to find your colonies
  If you insist on please; call the Italians
  Before you embark on you silly warmongers.
  **********************
  ምን ቋሚ ሰው አለ
  ።።።።።።።።።።።።።።
  ገበየሁ አባቴ አዎን ብለህ ነበር
  ቋሚ ሰው ተናገር
  ጀብዴን ለአለም አብስር
  ክንዴ እንደሰበረ የሞሶሌንን ቅጥር
  በአጭር እንደቀጨ የእብሪተኛን ሚስጥር
  በደስታ እንደሰጠሁ አጥንትና ደሜን ለኢትዮጵያ ክብር
  ገበየሁ አባቴ በአውነት ነው የምልህ
  እንዳንተ ፍላጎት ልክ እንደ ምኞትህ
  ምንም ቋሚ የለ
  በአባላጌ ጋራ በአድዋ የዋለ
  ጀብድህን ሊደግመው በአፅምህ የማለ
  አደራ ያልከውን ታሪክህን ሚጠብቅ
  መች ቋሚ ተገኝቶ ቃልህን አድምጦ በገድልህ ሚደምቅ
  ግን በተቃራኒው አጥንትና ደምክን በአንድ ላይ ቀይጦ
  ሌላ ደም ሚያስከፍል ቃላቶችን መርጦ
  በረቀቀ ዘዴ አገር ቆርጦ ሽጦ
  ደግሞ በላዩ ላይ ወደብ የሚመርቅ
  ለምን ባይ ጠያቂን ወገን ሚያሸማቀቅ
  በምስጋና ፋንታ ከርቸሌ ሚያማቅቅ
  ገድልህን አጥቁሮ ህገመንግስት ሚያረቅ
  አገር በቁም አስሮ በብሄር ሚራቀቅ
  በስርቆት በአፈናው በአድሎው ሚመፃደቅ
  እርኩስ መንፈስ በቅሎ የደምህን ወጤት ባንዲራን የሚል ጨርቅ
  እንኳን በክብር ሞትክ ይህንን ጉድ ሳታይ
  የሀገርክን መቸብቸብ የታሪክህን መጉደፍ በአብራክህ ክፋይ
  ገበየሁ አባቴ ምን ቋሚ ሰው አለ
  እንዳንተ አባላጌ በአድዋ የዋለ
  ገድልህን ሊደግመው በስምህ የማለ
  በሚያሳዝን መልኩ ቴዎድሮስ ዮሃንስ ሚኒሊክ እመየን
  ዘራይና እና አብዲሳ አቢቾ በላይን
  ብዙ ሰማዕታት እንዳንተ እንቁዎችን
  ነፍጠኛ በማለት ሚያጎድፍ ገድላችሁን
  የሀገር መጥፎ ህመም ከፋፋይ ታቅፈን
  ቋሚ ሰው የት ይገኝ ዘካሪ ታሪክን ጠባብ ትምክተኛ ፊውዳል ሳይባል ሚያነሳ ስምህን
  ገበየሁ አባቴ ምን ቋሚ ሰው አለ
  እንዳንተ አባላጌ በማይጨው የዋለ
  ሂድ ንገር ያልከውን
  ሚመሰክር ገድልህን
  አደራ ያልከውን የጠበቀ ቃልክን
  በእውነት ነው ምልህ
  ዛሬ ላይ አላይም የማለ በስምህ
  በሚያሳፍር መልኩ ጥላቻን የሚሰብክ
  ለዜጋው ማይራራ ለባህድ ሚብረከረክ
  የጎጥ ዛር አጓርቶ ግዑዝ ወንበር ሚያመልክ
  በብሄር ከበሮ በክልል ጥሩንባ
  ናላችንን ሚያዞር በነጋ በጠባ
  አፅምህን ወሮታል ከፋሽሽት ሚስጥሮ
  በጊዚያዊ ስልጣን በባህድ ዶላር ሰክሮ
  ወገን በቃኝ እሰኪል አንገት ደፍቶ ኑሮ
  በክብር እስኪቀብርህ ቋሚ ዘራፍ እስኪል በዋይተህ ተማሮ።
  ።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
  መታሰቢያነቱ: በህይወት ላሉ እንዲሁም ለአርበኛ ገበየሁ ጎራው እና ለሌሎችም አፅማቸው በዘመኑ የታሪክ ጉዶች ከተቀበረበት ተቆፍሮ ወጥቶ ለአመታት በአልባሌ ሁኔታ ለሚንከራትት የቁርጥ ቀን የኢትዮጵያ ሰማዕታት

 3. ዐፄ ፡ ምኒልክዬ ፤ የፋሽስት ፤ የባንዳና ፡ የዎሮ ፡ በላ ፤ ቅዠት ፤ ፤ ፤ የኢትዮጵያ ፡ ትራስ ፤ ንጉስ  ፤ ፤፤ ኩራቴ ፤ምቾቴ ፤ ሕይወቴ ፡ ምን ፡ ላርግዎት ???   አምልክ ፡ ከርስዎ ፡ ጋር ፡ ይሁን ። ድል ፤ ፍቅር ፤ ሰላም  ፡ ለኢትዮጵያ ። አሜን ።

LEAVE A REPLY