50 COMMENTS

 1. ዛሬ ጃፓንና አሜሪካ ከዚህ በፊት የነበረው ትውልድ የሰራውን ስሕተት ወደ ጎን ትተው
  እጅግ የጠበቀ ወዳጅነት ፈጥረው በሰላም ይኖራሉ።ጀርመንና ፈረንሳይ የጀርመን ናሺናል ሶሻሊስቶች በፈረንሳይ ላይ የፈጸሙት ስሕተት ዛሬና ወደ ፊትም እንዳይደገም አዲሱን ትውልድ በማስተማር ከሌሎች አውሮፓዊያን አገሮች በበለጠ ወዳጅ ሆነው አገሮቻቸውን ብቻ አይደለም አውሮፓን ለማሳደግ በጋራ እየደከሙ ይገኛሉ።እኛ አገር ደግሞ በተቃራኒው የምንከሳቸው ሰዎች ዛሬ የሚከሰሱበትን ጥፋት በትክክል ይስሩት አይስሩት በቂ መረጃ ሳይኖራቸው አጼ ምንሊክ እንዲህ አድርጎን፣አጼ ኃይለስላሴ ጨቁኖን እያሉ አጼ ምንሊክ ከመቶ ዓመት በፊት፣አጼ ኃይለሥላሴ ከአርባና ሃምሳ ዓመት በፊት ፈጸመውታል ብለው ለሚያምኑበት በቂ ማስረጃ ለሌለው ጥፋት የአሁኑን ትውልድ በመጥላት ከዚህ በፊት ተፈጽሟል ላሉት ጥፋት ከላይ የተጠቀሱት ነገስታት ተገኝተውበታል የሚባለውን ጎሳ አዲስ ትውልድ ተጠያቂ ሲያደርጉና ሲኮንኑ እስከዛሬ ይገኛሉ።ከላይ የጠቀስኩትን ዝም ብዬ ነገር ለማሳመር አላነሳሁትም።አንዳንዶች ስለዚች ኢትዮጵያዊ ነኝ ስላለችው ወጣት የሰጡት አስተያየት ስለገረመኝ ነው።ወያኔ ዘረኛ ምናምን ብለው የወያኔን ዘረኝነት ጥርሳቸው እስኪንገጫገጭ እየኮነኑ እነሱ ይቺን ልጅ ሻቢያ ከሰላሳና አርባ ዓመት በፊት ለሰራው ስህተት ተጠያቂ አድርገው ክፉ የዘረኝነት አስተያየት መስጠታቸው ዘረኞች ናቸው ብለው ከሚከሷቸው ቡድኖች የበለጠ አስትያየት ሰጪዎቹ ዘረኞች ሆነው ያገኘኋቸው ስለመሰለኝ ነው።ልጅቷን መቃወም ይቻላል።ምክንያቱም ልጅቷ እኔ ያልታየኝን ስሕተት ምናልባት ፈጽማ ሊሆን ይችላል። ያልገባትም ነገር ካለ በአግባቡ ማስረዳት ሲቻል ዘረኞችን እንቃወማለን እያልን እራሳችን የምንከሳቸው ቡድኖች ሰርተውታል ከሚባለው የበለጠ ስሕተት የምንስራ ከሆነ ከዚህ ስሕተታችን መታረም ይኖርብናል።አለያ ግን ሌላ ተልእኮ ይዘን የምንንቀሳቀስ ቅጥረኞች መሆናችንን ሊያስብቅብን ስለሚችል ብንጠነቀቅ ይሻላል። በተጨማሪ ልንረዳው የሚገባው ነገር ይህቺን ወጣት ኢትዮጵያዊ አይደለሽም ብሎ የመናገር መብትም እንደሌለን ነው።
  ቸር ይግጠመን!!!

 2. You are such a humble human being. I am 56 years old growing up in Ethiopia we had a lot of friends, neighbours and family members who married with Eritreans. I never saw them as anything else but Ethiopians above all lovely human beings who I loved and cared for very much. Just because politicians told us there side of story it does not change the lovely experience we had with each other. God bless you my lovely beautiful Eritrean/Ethiopian. If everything is good why are we dying trying to run away from our land. We must wake up and ask the question who is benefiting from our misery?

 3. የሰፈሬ ቆንጆ
  መልካም አዲስ አመት….!!
  መሲ.. .አማኑኤል መሳለሚያ የጨሰች
  የመርካቶ አካል.. ..
  በእህል በረንዳ.. ..በአውቶብሱ ተራ
  በኳስ ሜዳ ሠፈር በሙዚቃ ቤቶች በቡናና ኬክ ቤቶች
  በተከበበችዉ.. .ከፍተኛ 6 ቀበሌ
  01 አካባቢ ነዉ ተወልጄ ያደግሁት የትም እደግ አዱ ገነት ላይ ተወለድ መወለድ ካልቀረ ሸገር ኢትዮጵያ
  ትዝ.. .አለኝ ትዝ አለኝ
  …..እኔ ማነኝ?
  ኢትዮጲያዊ
  ወይስ አምቼ.. ..ለሚለው መልሴ
  ኢትዮጲያና
  ኤርትራ አንድ ናቸዉ በፖለቲካ ነዉ
  የተለያዩት.. ..አንቺ በእናቴም በአባቴም ኤርትራዊ ነኝ ባትይ ማን ይለይሽ ነበር
  …….ደምሽ ኤርትራዊ
  ትዉልድሽ ኢትዮጲያዊ ማለት ይቻላል
  ልዩነት ካለን
  ግን አንድ ነዉ ደማችን
  መልካችን
  ባህላችን
  እምነታችን
  ቋንቋችን …ማነው ኤርትራዊ? ኤርትራዊ ማንን ይመሥላል?
  ኢትዮጲያ ውስጥም ትግሪኛ
  ይነገራል ……That means doesn't matter what everybody say you are still …..
  ETHIOPIAN …..we are the same people…!!
  Keep proud to be Ethiopian
  GOOD LUCK!!!!!!!

 4. ግን ሰው ምንም መርሳት ይችላል
  እትዮጵያውነት ግን ምንም ብደረግ ምንም ብፈነቀል ከውስጥ ማውጣት የማይቻል ከሀቅም በላይ የሆነ ተፈጥሮ ነው
  ከእትዮጵያ መፈጠሬ ለዘላለም እግዚአብሔርን እያመሰገንኩ እኖራለሁ

Comments are closed.