50 COMMENTS

  1. ሰላም የእግዚኣብሕቤር ኃይል ከሁላችሑ ይሁን።መልካም ሥነ ምግባር በፍቅር በፅኑ ዕምነት በተስፋ የታነፁ ዓዋቂ ራዕይ የሆኑ መሪዎችና መምህራኖች የፍትሕና የሰላም መሐንዲሶች ናቸው።
     ለዕውነት የቆሙ በዕውነት የሚሠሩ መሪዎች ፣የፖለቲካ ሰዎች፣የሐይማኖት መምህራን፣የቀለም ኣስተማሪዎች ፣ ደራሲዎች፣ ተዋንያን፣ ዘፋኞች፣ ጋዜጠኞች፣ ወላጆች ሁሉ እግዚኣብሕቤር  ዕልፍ ያድርጋቸው፣የማያልቀውን ኃይል ብርታቱን ጥናቱን ዕውቀቱን ጥበቡን ኣብዝቶ ይስጣቸሑ። የዚህች ዓለም የፍትሕ የሰላም የጥበብና የብልፅግና መሐንዲሶች ናችሑ። በዛሬ ግዜ በተሳሳተ ርዕዮተ ዓለም ግዜ ገንዘብ ነው፣ገንዘብ የማይገዛው ነገር የለም፣ጉልበተኞችና ነጣቂዎች እንደ መኖር ሕልውና የሚታይበት ዓለም ላይ ብዙዎቹ በገንዘብ በካቲካላ በዝሙት፣ በዱቤ፣በውሸት፣ በዝርፊያ፣ በንጥቂያ፣በተንኮል፣በምቀኝነት፣በቅናት፣በፍርሃት  በጭካኔ በሽታ ሱስ ተይዘዋልና በኣጭር ግዜ ትምህርት ስለማይፈወሱ ለረጅም ግዜ ሳንሰለች በተለያየ ዘዴና በእግዚኣብሕቤር  ቃል ከሱሳቸው እስኪ ድኑ፣እስኪ ፀዱ ድረስ ኣጋጣሚውን ሁሉ እየተጠቀምን ደጋግመን ዕውቀትን ዕውነትን ከመስበክ  ከማስተማር ኣንቆጠብ።እየሱስ ያቀጣጠላቸው የእግዚኣብሕቤር ሻማዎች የዕውቀት የሕይወት ብርሃን ናቸውና ደምቀው ለዘላለም ይብሩ።መፅሐፍ ቅዱስም ዕውነቱን ማወቅ ኣለባችሑ ፣ ዕውነቱ ከሃጢያትና ከስቃይ ከህይወት ጨለማ ያወጣች ሑዋል ይላል ።ዕውቀት የህይወት ብርሃን ነው።ዕውቀት ወደ ዕውነት ይወስደናል።ዕውነትም እንዴት ኣድርገን መንፈሳችንን እንደምናጠነክርና በመንፈስ ኃይል እንዴት ጠረፍን ሁሉ ማንበብ እንደምንችል ይመራናል ።በዚህ ምድር ላይ እንደ እግዚኣብሕቤር ያደርገናል ፣ ወደ እግዚኣብሕቤር ቤት ወደ ሰማይ የምናርግበትን መንገድ ያሳየናል።ለዚህም እየሱስ የሠራው ተኣምር ምሥክሬ ነው።
    ኣስተማሪነት በጣም ትልቅ ብልሕነትን ትዕግሥትንና በዕውነት በዕውቀት በፈጣሪ ኃይል ላይ ፅኑ ዕምነት እንዲኖረን ያስፈልጋል።ከዕውነት የበለጠ ኃይል የለም።በዕውነት ለዕውነት ከሆነ ዕውነትም ሆነ ሕዝባችሑ ከጎናችሑ ነንና ምን ግዜም በርቱልን።ኣንድ ሰው በውስጡ ትንሽም ጥሩነት ካለው ይህንን ጥሩ ጎኑን እናበረታታዋለን።ምክንያቱም ተፈጥሮ እንደሚያስተምረን በፍቅር እየኮተኮትን ፈጣሪ በፈቀደው በዕውነት ኣስፈላጊውን ነገር እየሰጠን የተንከባከብነው ነገር ሁሉ በጣም እንደሚያድግ እንደሚለመልም ነው።ቅር ሳንሠኝና ተስፋ ሳንቆርጥ ካስተማርን ፣በህብረት እንደ ኢትዮጵያዊነት በትሕትና በትዕግሥት በመወያየት ሃሳብ በመለዋወጥ በመካከላችን ያለውን ዕምነትና ዕውቀታችንን ካዳበርን ወደፊት ይህችን ዓለም የሚያለሙ የሚያስዳድሩ ገነት የሚያደርጉ ብዙ ተዓምር የሚሠሩ እየሱሶችን እናፈራለን።  ለዕውነት የቆሙ በዕውነት የሚሠሩ ሰዎች ሁሉ ጀግኖች ናቸው።ጀግና በደልን ይፀየፋል እንጅ ሞትንም ኣይፈራም፣ለችግር ለመከራም ለኣሸባሪዎችም ለተንኮለኞችም ለተሳዳቢዎች ለባለጌዎች ለጉረኞ ለኣታላዮችም በጭራሽ ኣይበገርም።የሚሠሩ ኅጢያቶች ሁሉ የዕውቀት ማነስ ምልክት ነውና ለዕውነት የቆምን ጀግኖች ሁሉ ምንም ሳንረበሽ  ከመጥፎ ድርጊታቸው ዓለማወቃቸውን ተረድተን በትክክል ለመለወጥ ማስተማር ኣለብን።እየሱስም ኣሰቃይተው የሰቀሉት ላይ ሳይረበሽ ሳይናደድና ሳይጠላ በጣም የዕውቀት ማነስ እንደ ኣለባቸው ተረድቶ ኣባቱ ፈጣሪ እንዲምራቸው ከጥፋት እንዲያድናቸው እንዲያስተምራቸው ዕውነቱን እንዲገልፅላቸው የሚሠሩትን ኣያውቁምና ይቅር በላቸው ብሎ በመፀለይ ጀግንነት ዓዋቂነት ኢትዮጵያዊነት የእግዚኣብሕቤር ልጆች ማለት ምን ማለት እንደሆነና ሽልማቱም ዘላለማዊ ህይወት እንደሆነ ኣስተምሮናል። ምንም እንኳ ዛሬ ጥቂት ኢትዮጵያውያን ነን በሚሉ ዕውቀት ያነሳቸው ገብጋባ ሆዳሞች ስማችን ቢጎድፍም ኢትዮጵያዊነት ማለት የዚህችን ዓለም ህይወት የሚያጣፍጡ ጨዎች የዕውቀት የሕይወት ብርሃኖች ማለት ነው።ቶራም፣መፅሐፍ ቅዱስም፣ቁራንም ምስክሮቼ ናቸው።  በገብጋባነትና በእራስ ወዳድነት የተበከሉትን እንክርዳዶቹን ከመካከላችን ኣጥርተን ኢትዮጵያውያን ፈጣሪ እንደ ኣሰበን የዚህች ዓለም ሕይወት የሚያጣፍጡ ጨዎች ፣የሕይወት ብርሃኖች የምንሆንበት ይህችን ዓለም ገነት የምናደርግበት ፈጣሪን የምናኮራበት  ግዜ ይመጣል።ለሁሉም ግዜ ኣለው።ኢትዮጵያ ፅድቅ የፃድቃኖች ሃገር ነችና ኢትዮጵያና ህዝቦቹዋ ለዘላለም ይኖራሉ።
    ይህ ዕንቆቅልሽ ወይም ተረት ኣይደለም።ፈጣሪን ተቀብላችሑ በፅኑ ዕምነት ዕውነትን ከፈለጋችሑ ሁሉንም ትደርሱበታላችሑ፣ወደፊት ብዙ ተዓምሮችን ታያላችሑ፣ብዙም ተዓምሮችን ትሠራላችሑ።እግዚኣብሕቤር ከእኛ ጋር ነው፣ተስፋ ሳይቆርጡ ለዕውነት በፅኑ ዕምነት የጥየቁትን የለመኑትን እግዚኣብሕቤር ይሰጣል።ግዜው ደርሱዋልና እግዚኣብሕቤር ብርታቱን ፅዕናቱን ይስጠን። ።
    ራዕይን ከማጣት ሩሕን ማጣት ይሻላል ይላል የዓዋቂዎቹ የቅድመ ዓያቶቻችን ምስጥራዊ መልዕክት።ራዕይ ማለት በመልካም ሥነ ምግባር የታነፁ ዓዋቂ ዓርዓያ የሆኑ መሪዎችና መምህራን ማለት ሲሆን ሩህ ማለት ደግሞ ምግብ ማለት ነው። ምንም እንኳን ግዜው በሃዘን በስቃይ የተሞላ ቢሆንም ቃል ኃይል ስለኣለው መልካም ነገር በመመኘት መልካም ኃይል እንዲፈጠር በፍቅር የተሞላ የሰላም የደስታ የጤና የህብረት የብልፅግና ግዜ እንዲመጣ በድምፃችንና በመንፈሳችን ኃይል ቤታችንን ሠፈራችንን ኣካባቢያችንን ሃገራችንን ዓለማችንን መከተብ እንችላለን ።መጭው ግዜም እንደ ኣልማዝ ዘላለማዊ የሆነ ሰላም ጤና ደስታ ፍቅር ህብረት ለጋስነት ብልፅግንና እንደ ኣባት ኣብራሃም ብዙ መቶ በፀጋ የተሞሉ ዕድሜዎችን  እንመኛለን።ያዘኑትንም ኣይዞዋችሑ ሰላምና ፍትሕ የሚነግሥበት መንፈስ የሚታደስበት ደስታ የሚሰፍነበት ፀጋ የተሞላበት ግዜ መምጫው ደርሱዋል በሉልን ።
    በዚህ ኣጋጣሚ ልጠቁማችሑ የምፈልገው መሐይም የሆኑ ኣጭበርባሪዎች የነገሩንን ዝም ብለን መቀበል ሳይሆን እራሳችን ተፈጥሮን ኣጥንተን ተመራምረን ማንበብና ዕውነቱ ላይ መድረስ ወይም ከታሪካችን ከዓያቶቻችን ለመማር ለመረዳት ዕውነቱ ላይ ለመድረስ መሞከር መነሳት ኣለብን።ብዙ ግዜ ዓለማችንን ባለማወቅ ጌታችን እየሱስ ጥቁር ቡናማ የቆዳ ቀለም እንደነበረው በሙሉ ልባችን መናገር ኣልቻልንም።እንደውም ብዙ ወንድሞቻችንና እህቶቻችን ዓለምን እንዳያነቡ እንዳያውቁ በውሸት ፕሮፓጋንዳ ታውረው እየሱስን ነጭ ወይም ቢጫ ኣድርገው የራሳቸውን ወገናቸውን እንዲጠሉና የኣጭበርባሪዎች መጠቀሚያ  ወዶ ባሪያዎች ሆነዋል።እየሱስ መካከለኛው ወይም ሰሜን ኣውሮፓ የተወለደ ቢሆን ኖሮ ነጭ ወይም ቢጫ ነው ብለው ቢሉን ኖሮ ይሁንላቸው ብለን መቀበል እንችል ነበር።ኣጋዘን ሚዳቆና ፍየል ሁሉም ከደምና ከሥጋ በሠሩም በመካከላቸው ግን ትልቅ ልዩነት እንዳላቸው ሁሉ ጥቁሩ ቡናማው፣ቢጫው፣ነጭ ሕዝቦች ከደምና ከሥጋ ቢሠሩም በሰውነታችን ችሎታ ትልቅ ልዩነት ኣለ።ጥቁሩና ቡናማው የቆዳችን ቀለም የፀሐይ ጨረር መከላከያና ሙቀት መቆጣጠሪያ ብቻ ሳይሆን ዕውቀትና ኃይልም ማጠራቀሚያ ነው።ከፈጣሪ የተሰጠን በጠረፋችን ያለ ዕውቀትና ጥበብ ሁሉ ተጠራቅሞበታል።እግዚኣብሕቤር ይህንን ያደረገው ለታላቅ ተግባር ማለትም ለዚህች ምድር ህይወትን የምናጣፍጥ ጨው ፣የዕውነት ብርሃን ፣ኣልሚና ኣስተዳዳሪ እንድንሆን በማሰብ ለትልቅ ኃላፊነት ነው።ይህንን ስል ጥቁሩንና ቡናማውን ሕዝብ ለማዳነቅ ወይ የበላይ ለማድረግ ኣይደለም።በዕውነት ነው የምላችሑ ጥቁሮቹና ቡናማዎቹ ችሎታው ኣለን ብለው ሌሎችን ሲበድሉ ወይም ከሌሎች በላይ ለመሆን ሲሞክሩ ማየት ኣልፈልግም።በሌላም በኩል ደግሞ ጥቁሩና ቡናማዎቹ እግዚኣብሕቤር ኣድሎ በሰጣቸው ችሎታ ዓለምን እንዳያለሙ እግዚኣብሕቤር እንዳያገለግሉ በውሸት ታውረው ኣታውቁም ተብለው በዕውቀት ከእነሱ በጣም ከሚያንሱ ሰዎች ሥር ባሪያ ሆነው የሰው እጅ ኣይተው ሲኖሩ  ወይም ለኣጭበርባሪዎች ለጥፋት መጠቀሚያ ሆነው ማየት ኣልፈልግም። ሳንኮራ ወይም ሳንቀና እግዚኣብሕቤር የፈጠርውን ኣክብረን ተግባራችንን ስናከናውን ብቻ ነው በሰላም በጤና በደስታ በመኖር ብዙ ተዓምሮችን በመሥራት መበልፅግና እግዚኣብሕቤር ማድነቅ ወይም እንደ እግዚኣብሕቤር መሆን የምንችለው።የጥበብ መጀመሪያ እግዚኣብሕቤር መፍራት ነው ይላል መፅሐፍ ቅዱስ።ተፈጥሮን በማንበብ እግዚኣብሕቤር ማክበር ብልሕነት የሰባዊነት የዓዋቂነት የኢትዮጵያዊነት ምልክት ነው።ምከሩ ተማከሩ ኣስተምሩ።ኣቦ ይመቻችሑ።
    ፍፁም የማይሳሳት ፈጣሪ ብቻ ነው።ስለዚህ ኣምልጠው የገቡትን ሥህተቶች እያረማችሑ ኣንብባችሑ ሃሳቤን ለመረዳት ሞክሩ።ኣንዳንድ ግዜ ኣንድ ሲደመር ኣንድ ብለን ሁለት የፃፍን መስሎን ሶሥት እንፅፋለን።
     ምን ግዜም ተስፋ ሳትቆርጥና ሳትሠለች በዕውነት ለዕውነት እንሥራ።በዕውነት ለዕውነት የሚሠራ ቤተሰቡንና
    ህብረተሰቡን የሚያገለግል ጀግና ነው።ዕውነትም የጀግና ጋሻ ነው።ከዕውነት የበለጠ ኃይል የለም። ዕውነት ዕውቀት ነው፡ጭንቅላታችንን የበለጠ ያዳብረዋል።ዕውነት እግዚኣብሕቤር ነው።ኃይል የእግዚኣብሕቤር ነው።
    የጉንዳን ጉልበት ይሥጠን፡እንደ ንብ ታታሪ ያድርገን፡እንደ ዔሊም ብልህ ያድርገን፡መንፈሳችንም የጠነከረ ጠረፍን የሚያነብ ይሁን።
    የእስራኤል ኣምላክ መንፈሱ ተነስቱዋል፡የኣብራሃም የሲሳይ ቤት ያድርግልን፡እግዚኣብሕቤር ታላቅ ነው ።
    ሰላም

Comments are closed.