50 COMMENTS

  1. The professor is preaching TPLF ideology with no facts and truth in it. This is nonsense which I do not expect from an educated person. This is wicked personality being led by ego and emissions. In the discussion, Prof Ezkel was asked about what did the Amhara benefit from the previous rulers. His response was that the Amhara group did not benefit but others were harmed.  This is narrowed thinking with no sense of humanity. The mess was happening from the rulers and no any group benefited from the previous dictators.

  2. ህብር አራዴዎን በጣም የሚመሰገን ሰራ ነው እየሰራችሁ ያላችሁት

  3. "በላይ ዘለቀን ሃይለስላሴ ሰቀሉት የሚባለው ውሸት ነው" ስትል፥ አቻም ምን ለማለት ፈልገህ ነው? እዚህ ላይ የምን ግዜም ክህደት ፈጽመሃል! በጣም ወደ ጅልነት ወረድህብኝ ጓዴ!

  4. አማርኛ የስራ ቋንቋ እንዲሆን ያደረጉት ከትግራይ የተንበይ ተወላጅ የነበሩት ትግርኛ ተናጋሪው አፄ ዮሀንስ ነበሩ። በዘመነ መሳፍንት ጊዜ የተፈጠሩት ትንንሽ መንግስቶች ከውጭ አጋሮቻቸው ጋር የሚሰሩበት ቋንቋ አማርኛ ነበር ቢሆንም የስራ ቋንቋ እንዲሆን በአዋጅ ደረጃ የተወሰነው በአፄ ዮሀንስ ዘመን ነው። አማራ ከአማርኛ ጋር የሚዛመደው በቋንቋው ብቻ ነው በተረፈ የባህል ጫና ፈጥሮብናል፣ጨቋኝ መንግስት ነበር የሚባለው ነገር የመጣው ጣሊያን ከፋፍሎ ለመግዛት የተጠቀመበት ዘዴ ነው የሚገርመው በወቅቱ አባቶቻችን ንቃተ ህሊናቸው ከፍ ያለ ሰለነበር በዚህ አወናባጅ ድብቅ ሴራ አልተሸነፉም የዚህ ዘመን ትውልዶች ግን ውሀ በማይቋጥር ትርክት ባለማስተዋል እንባላለን ።የጨቋኝና የተጨቋኝ የበላይና የበታች ስሜትን የፈጠሩብን ጠላቶቻችን ናቸው!!

  5. ለማንኛውም ጥሩ ጅማሬ ነው የፕሮፌሰር ሕዝቅኤልን e mail ባገኝ አጼ ሃይለስላሴ። ጋላ ነኝ ያሉበትን ማስረጃ እልክለት ነበር። አድራሻው ያላችሁ ተባበሩኝ።

  6. ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል እንዴ በላይ ዘለቀ ለምን ተገደለ የሚለውን እኮ መተረክ የሚችለው ሕዝብ አይደለም እንዴት ለእርቅ ተጠርቶ ለእስር እንደበቃ ከዚያስ እስር ቤት ምን ተፈጸመ ማን ምን አደረገ የሚለውን የተረኩት ውስጥ የነበሩ ናቸው።

  7. ፕሮፌሰር ሕዝቅኤል የማታስተውለው ነገር ጋላ ወይም ወላሞ ጉዴላ የመባሉ ቃላት በአማርኛ ትርጉም የላቸውም። ለምሳሌ ከኦሮሞ መስፋፋት ቀደም ብሎ ጋላ አይታወቅም፣ የወላይታ ሕዝብ ወላሞ ብሎ ካልተናገረም ከየት ያመጡታል?

  8. እንዲህ ዓይነት የታሪክ እውነታዎችን በማስረጃ መወያየት ያስፈልጋል። ላለመካካድ ተጨባጭ ማስረጃዎች ያስፈልጋሉ።

  9. በድሮ ፖለቲካ ላይ መነታረክ ወሲብ በኮንዶም እንደመፈጸም ይቆጠራል፡፡ ምክንያቱም ዝም ብሎ ልፊያ ብቻ ነው ፍሬ የለውም፡፡ ምንአልባት ፍሬ እንኳ ቢኖረው አሁን ያለውን ህዝብ ህይወት እና ሰላም ማሳጣት ብቻ ነው፡፡ስለዚህ የኢትዮጵያን ፖለቲካ ወደ ዃላ እንደግመል ሽንት ያውም በቅጥፈት ላይ በተመሰረተ ፕሮፓጋንዳ የምትወስዱ የአስተሳሰብ ደሀጣን ከኢትዮጵያን ፖለቲካ ገለል ብትሉ የህዝብን ጫና መቀነስ ይቻል ነበር፡፡ ከዚህ በተጨማሪ የኢትዮጵያን ህዝብ በቋንቋ እየሰፈሩ ማጋደል እና ማጣላት ምሁረነት አይደለም፡፡

    የሰው ልጅ የራሱን ሂወት ከሚያወሳስብባቸው ነገሮች አንዱ ሰውነቱን ሰዎች በምድር ላይ ሲኖሩ ከሚጠቀሙባቸው የተግባቦት ስልቶች፣ አመጋገብ ስርአቶች፣በደስታ ግዜ ከሚያወዛውዛቸው ሰውነት አካላቶች እንዲሁም የማእድ ቤት ቁሳቁሶች አሳንሶ ማየቱ ነው፡፡ በአሁኑ ሰአት ሀገራች እያራመደች ያለው ስርአት ይህ ነው፡፡ ሕገመንግስቱን ጨምሮ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ያሉ ተዋንያን በሙሉ ህዝቡን የሚሰፍሩት በሰውነቱ ሳይሆን አፉን በፈታበት ቋንቋ ነው፡፡ ሰው ምድር ላይ ካሉ ፍጡራንም ሆነ የሰው መገልገያ ቁሳቁስ በላይ ነው፡፡ ስለዚህ ለሀገራች የሚበጃት በዜግነት ላይ የተመሰረተ የመንግሰት አስተዳደር ነው፡፡ መንግስት ለአንድ ሐገር የሚስፈልገው የመንግስት አገልግሎት ለህዝቡ ከማድረስ ያለፈ ሌላ ፋይዳ የለውም፡፡ ስለዚህ የሀገሪቷን አደረጃጀት የመንግስት አገልግሎት ለህዝቡ ተደራሽ ከማድረግ አንጻር ቢሆን እና ማንኛውም ዜጋ በየትኛውም አካባቢ በሚፈልገው ቋንቋም ሆነ ሌላ መገልገያ መጠቀም እንዲችል የሚስችል አደረጃጀት ቢፈጠር የተሻለ ይመስለኛል፡፡

    ሌላው ላለፉት 26 አመታት የተሰበከው የተንሸዋረረ የበዳይ ተበዳይ ትርክት ሊስተካከል ይገባል፡፡ የቀድሞ ኢትዮጵያውያን ስኬታቸውም ሆነ ጥፋታቸው የጋራ ነው፡፡ አብረው ላለሙትም በጋራ ሊወደሱ አብረው ላጠፉትም በጋራ ሊኮነኑ ይገባል መኮነን በአሁኑ ሰአት ካስፈለገ፡፡ በነኢዝቄል እና መሰሎቹ እይታ ግን ጥፋታቸው የአንድ ወገን ብቻ ስኬታቸው ግን የጋራ ነው ፡፡ ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ የትኛውም ህዝብ መርጦና ፈቅዶ የፖለቲካ መሪዎቹን አስቀምጦ አያውቅም ስለዚህ የዚህ ህዝብ ገዢ መደብ የዚያ ህዝብ ገዢ መደብ እያላችሁ የደሃውን ህዝብ ኑሮ ማክበዳችሁ የምሁር ደሃጣን መሆናችሁን ያሳያል፡፡ በዚህ አባባላችሁ ምክንያት የስንት ንጹሀን ዜጎች ህይወት በከንቱ እንዲያልፍ ሆኖአል እያለፈሰ ይገኛል?. በእርግጥ በአሁን ሰአት የህዝብን ስም ለፖለቲካ ማህበር ስምነት መጠቀም የተለመደ ሆኖአል፡፡ ይህ ተግባር ግን እጅግ ዚበዛ ሊወገዝ የሚገባው እና ህዝብ አምርሮ ሊታገለው የሚገባ ተግባር ነው፡፡ የየትኛውም ህዝብ ፈቅዶ እና መርጦ የፖለቲካ ማህበሮችን በስሜ ተጠሩ ብሎ ፈቅዶ አያውቅም፡፡ በጎሳ ስም የተደራጁ የፖለቲካ ማህበሮችም በራሳቸው ፖለቲካ አስተሳሰብ ስለማይተማመኑ የጎሳን ስም ይጠቀማሉ፡፡ ይህ ድርጊት እጅግ ዃላቀር እና የፖለቲካ ማህበሮች ስልጣን በያዙ ግዜ ለሚፈጽሙት ኢሰብአዊ ተግባር የተጠቀሙትን የጎሳ ስም በሌሎች ማህበረሰቦች ዘንድ የተጠላ እና የተገለለ እንዲሆን እያደረገ ይገገኛል፡፡ ስለዚህ የየትኛውም የኢትዮጵያውያ ቋንቋ ተናጋሪ ማህበረሰብ ይህን ድርጊት አጥቡቆ ሊታገለው ይገባል፡፡

    የኢትዮጵያ ህዝብ በኢኮኖሚ ደሀ ነው ነገር ግን በማህበራዊ ትስስር እና ተከባብሮ እና ተማምኖ አብሮ በመኖር ግን እጅግ ሲበዛ ሀብታም የሆነ ህዝብ ነው፡፡ ላለፉት 26 አመታት በተራመደው ፖለቲካ ምክንያት ግን ይህንን ሀብቱን እየተነጠቀ ይገኛል፡፡ ለዚህም ማሳያ የሚሆነው በያካባቢው የሚታዩ ቋንቋ ተኮር ግጭቶች ናቸው፡፡ አሁን አሁን እማ የሰካራም የመሸታ ቤት ግጭቶች እንኳን ቋንቋ ተኮር እየሆኑ መምጣታቸው ልብ ይሏል፡፡ከዚህ በፊት በተንሸዋረረ የበዳይ ተበዳይ ትርክት ምክንያት በበዳይነት የተፈረጀው ህዝብ አደን በሚመስ መልኩ በሁሉም የሀገሪቶ ክፍሎች ሲፈናቀል፣ሲገደል እንዲሁም ክብሩ ሲዋረድ ኖሮአል፡፡ አሁን ደግሞ ይህ አደገኛ የአስተሳሰብ ውጤት አድማሱን እያሰፋ በሌሎች ዜጎችም ላይ በ መቶ ሺህ የሚቆጠር ህዝብ እስከመፈናቀል ያደረሰ እና የሰው ህይወት የቀጠፈ ሁናቴ ተፈጥሮአል፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ዜጋው በአፍ መፍቻ በቋንቋ ምክንያት ጎረቤት ጎረቤቱን ይፈራዋል፣ባል ሚስቱን ሚስት ባልዋን ትፈራለች፣ ጎደኛ ጎደኛውን አያምነውም፡፡ ስለዚህ ሀገር ማለት በአብዛኛው ሰው ከሆነ በዚህ የመንግስት ስርአት ምክንያት እና የአንድ ቋንቋ ተናጋሪ ህዝብ ተቆርቋሪ ነን በሚሉ ምሁር ነን ባዮች ምክንያት ሀገራችንን እያጣን ነው ማለት ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪም በባዶ ሆዳችን ላይ ጥላቻና ዘረኝነት ተጨምሮበት የህዝብን ህይወት እጅግ የተወሳሰበ እንዲሆን ሆኖአል፡፡

    ሌላው ኢትዮጵያን አደጋ ውስጥ እየጣለ ያለው ነገር የመንጋ አስተሳሰብ በእጅጉ እየዳበረ መምጣቱ ነው፡፡ የመንጋ አስተሳሰብ ማለት ሰዎች በመሰረቱት መንጋ ውስጥ ያለን አሉታዊም ሆነ አወንታዊ አስተሳሰብ ምንም ሳይመረምሩ መቀበል እና ማስተጋባት ማለት ነው፡፡ ይህ አደገኛ አስተሳሰብ በተለይም እጅግ ስነምግባር እና ሀላፊነት በጎደላቸውና አእምሮአቸው ባደፈ የመንጋ መሪዎች በሚቀነቀኑ አደገኛ ፕሮፓጋንዳዎች ምክንያት የብዙ ዜጎች ህይወት አደጋ ላይ እንዲወድቅ ሆኖአል፡፡ ፈጣሪ የ ሰውን ልጅ ሲፈጥር በመንጋ እንዲያስብ ፈልጎ ቢሆን ኖሮ አንድ አንደ አእምሮ አይሰጠንም ነበር ወይም ለመሰረትነው ቋንቋን መሰረት ያደረገ መንጋ አንድ አእምሮ ለብዙ እጅ እና እግሮች እነዲሁም የተለያየ የሰውነት አካል አንድ ጭንቅላት ብቻ ይሰጠን ነበር፡፡ ይህም የሚያሳየው ይህ አስተሳሰብ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን እርስበርስ እንዲጓተቱ እና ትርምስ ውስጥ እንዲገቡ እያደረገ ይገኛል፡፡ ስለዚህ ኢትዮጵያን እና ህዝቦቿን ከመንጋ አስተሳሰብ ተጋላጭነት ነጻ የሚያወጣ ዜግነትን መሰረት ያደረገ ዘመናዊ የፖለቲካ አደረጃጀትን መገንባት ያስፈልጋል፡፡

    ኢትዩጵያ ለዘላለም በክብር ትኑር

Comments are closed.