50 COMMENTS

  1. ኡፍፍፍፍ መለያየት ስሙ እናሱ ሲያስጠል እኔም ዛሬ ከምወደ ፍቅርኛየጋ ተለያየው ኡፍፍ በሉ ፋኑኤል እና መቅደስ ተለያዩ በሉ ቻሉት እግዲ መቸም የማይቻል ነገር የለም በዚች ምድር ላይ

  2. ተወልጄ ያደኩት ክፍለ-ሀገር ነው አሁን ግን የምኖረው በሳውዝ አፍሪካ ነው፡፡
    ከክፍለሀገር ወደ አዲስ አበባ ስመጣ ዘመድ ሊያስተምረኝ በሚል ሰበብ ነበር የመጣሁት ፡፡ ነገር ግን ከዚህ ዘመዴ ጋር መስማማት አልቻልንም ማለትም ይሄ ዘመድ ተብየው በጣም ሀብታም ነው በዚህም ጸጉር ቤት ነበር ከፍሎ የሚያስተምረኝ፡፡ ታዲያ ሚስቱ መውለድ አትችልም ነበር ለዛም ነው ለካስ እኔን ያሰበው እንደ ሁለተኛ ሚስት አድርጎ ቤት ገዝቶ ሊያኖረኝ ነበር፡፡
    እኔ ግን ይሄን ነገር ህሊናዬ አልተቀበለውም ነበር ምክንያቱም ከገዛ ከዘመዴ ጋር እንዲህ አይነት ጸያፍ ነገር መፈጸም አልፈለኩም ስለዚህ ማንም ሳያያኝ ተነስቼ ጠፋሁና ካራ
    (አዲስ አበባ) አካባቢ ቤት ተከራይቼ መኖር ጀመርኩ::
    እናም በዚህ ወቅት ነበር በታክሲ ሹፍርና የሚተዳደረውን ፍቅረኛዬን የተዋወኩት፡፡
    እናም ያኔ ተቀራርበን በፍቅር እየኖርን እስከ ተለያየንበት እለት ድረስ እሱ በጣም ጥሩ ሰው ነው በቃ ምን ልበላችሁ በወቅቱ ለኔ የተሰጠኝ ውድ ስጦታ እስኪመስለኝ ድረስ ነው የተሰማኝ፡፡
    በአጋጣሚ ኮንዶሚኒየም ቤት ተመዝግበን ነበርና እጣው ሲደርሰን ቤቱን አከራይተነው እኛ ግን ወደ ኮተቤ መስመር አከባቢ ተከራይተን እንኖራለን፡፡
    እንዲህ እንዲያ እያልን ለ3 ዓመታት በአንድ ቤት ውስጥ አብረን መኖር ጀመርን፡፡
    እሱ የታክሲ ሾፌር ነው፡የታክሲ ሹፌር ሲኮን ደግሞ የምታገኝበትና የምታጣበት ጊዜ አለ ፡፡
    ይህም አልቀረ አሰሪዎቹ እሱን ከስራ አሰናበቱት ታዲያ በዚህ ወቅት በቤታችን የሚበላና የሚጠጣ ለማግኘት እየተቸገርን ፈተና ውስጥ ገባን፡፡
    እኔ ለዚህ ፍቅራችን ስል ብዙ መስዋእትነት ከፍያለው ጌጣጌጦቼን ሸጫለው ሰው ቤት ተመላላሽ ሆኜ በመስራት ለፍቅራችን አቅሜ በፈቀደው ደፋ ቀና ለማለት
    ሞከሪያለው፡፡
    በዚህ መሐል ግን አንድ ሀሳብ መጣልኝ፡፡ ለምን የሰው ሀገር ሄጄ ሰርቼ ትንሽ የሆነ ነገር አንይዝም የሚል እናም ከእሱ ጋር ተነጋግረን ተግባባንና ተነስቼ ወደዚህ(ሳውዝ አፍሪካ) መጣሁ፡፡
    በየቀኑ እንደዋወላለን የወር ደሞዜንም ወዲያው ነበር የምልከው እናም እኔ እየሰራው በምልክለት ገንዘብ የቤት እቃዎችን እያሟላ ቤታችን ማሳመር ጀመረ ይሄኔ ወደ ሀገሬ መሄድ መናፈቅ ጀመርኩ በጣም ጓጓው፡፡
    እኔ እዚህ በስራ ጫና እጅግ ተወጥሬ እየሰራው ነገን ተስፋ አድርጌ የሚሰጡኝን ገንዘብ ተበድረንም ቢሆን ጨምረንበት አንድ ታክሲ መግዛት አለብን እስከመቼ
    የሰውን ይይዛል እያልኩ እንደገና በየመሃሉም አንዳንድ የቤት እቃዎችን አሟላ እያልኩ ገንዘብ እልክለት ነበር፡፡ በሱ ምክንያት ከቤተሰብ; ከዘመድአዝማድና ከጓደኞቼ ሁሉ ተቆራርጪያለው፡፡
    እስካሁን ድረስ ይሄን ሁሉ ሆኜለት እየኖርኩ ነበር፡፡
    ወደ ሳውዝ አፍሪካ ከመጣሁ በኋላ ያሰብኩት ተሳክቶ ከሱ ጋር ህይወታችን አምሮና ተስተካክሎ የምንኖርበት ወቅት ነበር የምናፍቀው፡፡ ለካስ እኔ ወደዚህ መጥቼ
    2 አመት ሳይሞላኝ ነው እሱ ሌላ ሴት የለመደው፡፡
    አብረን ተከራይተን የምንኖርቤት ቤት አከራዮች በጣም ጥሩ ሰው ናቸው ሁለታችንንም በጣም ይወዱናል ታዲያ እኚህ አከራዮቼ በመኃል ይደውልሉኝና ቤት ሊቀይር እንደሆነ ነገሩኝ፡፡
    ፈጠን ብዬ ወደሱ ደወልኩና ለምን ቤቱን እንደሚለቅ ብጠይቀው አንቺ ልትመጪ ስለሆነ ደህና ቤት ተከራይቼ ልጠብቅሽ ብዬ ነው በዛ ላይ ያ ኮንዶሚኒየም ቤታችን
    ወደ 3000 ሺህ ብር ስለተከራዬ በዚህ ብር ደግሞ እኛም ወደ ሀያት አካባቢ ሌላ ኮንደሚንየም እንድንከራይ ፈልጌ ነው አለኝ ቅር እያለኝም ቢሆን በሀሳቡ ተስማማው
    እንዳለው ወደ ሐያት መንደር አካባቢ ኮንዶሚኒዬም ተከራይቶ መኖር መጀመሩን ነገረኝ፡፡
    ባይገርማችሁ በህልሜ ዘወትር አልጋችን ተሰብሮ አይ ነበር፡፡

    ለካስ እኔ አመሻሽ አከባቢ ሁሌ ስደውልለት የሚያናግረኝ አብራው ያለችው ሴት እንዳትሰማበት በሚል ነው መሰል ወደ ውጪ እየወጣ ሲያናግረኝ እንደነበር ካለፈ በሃላ አከራዮቼ ነበሩ የነገሩኝ፡፡
    በዚህ መቼ አበቃና አንድ ቀን አንዲት ጎደኛዬ ደወለቺልኝና ምን ሆናችሁ ነው ? ተጣልታችሁ ነበር እንዴ? ባልሽ እኮ ቅዳሜ እለት ድል ባለ ሰርግ አገባ ብላ ነገረቺኝ፡፡አዲስ ከጀመረው ፍቅረኛው ጋር ተጋብቶ???
    በጣም የሚገርመው እስከ ቅዳሜ እለት ድረስ ስደውልለት እንደሚያፈቅረኝና ከኔ ውጪ ሌላ ሴት ማየት በፍጹም እንደማያስብ ይነግረኝ ነበር፡፡
    ታዲያ እቺህ ጓደኛዬ የሱን ማግባት ስታረዳኝ ስሜቴን መቆጣጠር ተሳነኝ ባጋጣሚ ፎቅ ላይ ነበርኩና እራሴን ስቼ ተንከባልዬ ወደኩ በዚህም በአካሌ ላይ ከፍተኛ
    ጉዳት ደረሶብኝ ስለነበር በአሰርዮቼ አማካኝነት ሆስፒታል ተኝቼ ለተወሰኑ ወራት ያህል ህክምና ተደርጎልኝ እንደ ፈጣሪ ፈቃድ ህይወቴ ልተርፍ ችሏል፡፡

    ቀን ለሊት ሳልል ነጭ ላቤን አንጣፍፌ ያገኘሁትን ገንዘብ ለሱ ልኬ ከዛሬ ነገ ለመሄድ ተዘጋጅቼ የነበርኩት ሰው መና አስቀረኝ ስንት ያለምኩትን ህልሜን ከትቢያ ቀላቀለው ተስፋዬንም አጨለመው እናም አሁን ብታምኑም ባታምኑም በእጄ ላይ አምስት ሳንቲም እንኳን የለኝም፡፡
    እናትና አባቴ በህይወት የሉም ነገር ግን ሁለት ወንድሞች አሉኝ፡፡ በደህናው ጊዜ እነሱን እንኳን መርዳትን ዘንግቼ ነበር፡፡
    እድሜዬም እየሄደ 28 ዓመት ሆኖኛል፡፡ ይህ ሰው በእድሜዬ; በጊዜዬ; በገንዘቤና በማንነቴ ላይ ተጫውቶብኝ ሄደ፡፡

    በሀገር ውስጥም ይሁን ከሀገር ውጪ የምትኖሩ እህት
    ወንድሞቼ የማደርገው ጠፍቶኝ ህይወቴን እንዴት
    ማስተካከል እንዳለብኝ ጨንቆኛል እናም እባካችሁ
    ወገናዊ ሀሳባችሁን አካፍሉኝ፡፡

  3. Joni enidene tiru neh yerasihin nibiret seteh balaweqe chal aderekew koki gin ke hulet and yata satihogni atiqerim merach yiwediqal ketemerach joni zor bileh enidatayat kokin

LEAVE A REPLY