▽ Subscribe Youtube channel Ethiopa Tube to watch the news every day
➞ Youtube : https://goo.gl/pAFiq9
Home
VOA Amharic Radio Daily News Saturday September 15 2018
▽ Subscribe Youtube channel Ethiopa Tube to watch the news every day
➞ Youtube : https://goo.gl/pAFiq9
አረንጓዴ-ብጫ-ቀይ ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ የኢትዮጵያ የነፃነት አርማ እንጅ የማንንም ጅርጅት የሚወክል አይደለም፡፡
ግንቦት 7 እና ሌሎች ወደአገር ሲገቡ የግል አርማቸውን በየቦታው አልሰቀሉም፤ አረንጓዴ-ብጫ -ቀይ የኢትዮጵያ እንጅ የማንንም ድርጅት ወይም ጎሣ ወክሎ የቆመ አይደለም፤ በአርንጓዴ በጫ ቀይ ላይ የተጨመረውን የነገሥታቱንም ሆነ የደርግን አርማ ሕዝብ አልተጠቀመበትም፤ የገዥወች አርማ ያልተጨመረበትን ነው ሕዝቡ በክብር ከፍ አድርጎ ከወራሪወች ጋር እየተዋደቀ አገሩን ከወራሪወች ጠብቆ የኖረው፡፡ ለውጡን ለመደገፍ በተደረጉት ሰልፎች ሁሉ ሕዝቡ አረንጓዴ ብጫ ቀይ ሰንደቅ ዓላማ ይዞ የወጣው ኢትዮጵያን እንጅ ድርጅትን ወክሎ አይደለም፡፡ የኦነግ ባንዲራ ግን የኦነግን ዘረኛና የግንጠላ ዓላማ ብቻ የሚወክል በመሆኑ ሁለቱን ማወዳደር አይቻልም፤ ኦነግ የኦነግ አባላትን እንጅ መላውን የኦሮሞ ሕዝብ አይወክልም፤ የኦነግ አባላትና ሰርጎ ገቦች የፈጠሩትን ረብሻ የቄሮ አስመስሎ ማቅረብም ታላቅ ስህተት ነው፤ በሌላ በኩልም ጅቦቹ ቀደም ሲል ተለጣፊ ቄሮና ፋኖ አስርጎ ለማስገባት ጀምረው እንደነበር መገንዘብና መጠንቀቅ ያስፈልጋል፡፡ በአንዳንድ አካባቢ ወጣቶች ዘንድ የሚታየው አረመኔአዊና ዘግናኝ ድርጊት ከአረመኔ ጅቦች ጋር የተየያዘ ሊሆን ይችላል፡፡ ቄሮ የታገለው ለኦነግ ጠባብና አገር አፍራሽ የወየኔ ዓይነት ዓላማ አይደለም ፤ ጀዋር በብልጥነት ለማምታታት አትሞክር፤ ኦነግ ከፀረ ኢትዮጵየዊነትና ከጠባብነት ቫይረስ ማገገሙን በተግባር ማረጋገጥ ይጠበቅበታል፤ በጠመንጃ ያጣውን ግንጠላ አሁን በማታለል ለመጠቀም ፈልጎ ከሆነ ብልጠቱ የትም አያደርሰውም፤ ሕዝብ ቀድሞት ነቅቷል፡፡ ሁሉም በዕኩልነት ለሚኖሩባት አገር ግንባታ ቢቆም፥ ቁም ነገር ሠርቶ ታሪኩን ሊያድስ ይችላል፤ ያለዚያ ፀረ ሰላምና ፀረ ሕዝብ እንደሆነ እንደወያኔ መሞቻው ይደርሳል፡፡ ይህ ደግሞ የሞት ሞት ነው፡፡ 40 አመት ሙሉ መማር
አለመቻል፡፡ ከለውጡ ወዲሕ በሚደረጉ ሰልፎች የኦነግን አርማ እያውለበለቡ የኦነግ አባላትና ደጋፊወች ያለምንም ችግር ሲሰለፉና ሚሊየኔም አዳራሽ ሳይቀር እያውለበለቡ ሲደሰቱ ማንም አልተቃወመም፤ ችግሩ የተፈጠረው የኦነግን አርማ ለመስቀል ሌላውን ማውረድና መጣል፥ መንገድ፥ አጥርና የኤሌክትሪክ ምሰሶወችን፥ የግለሰብ በርና አጥር … መቀባትና «የእኔ ብቻ» መሆን አለበት ከሚል የመነጨ ነው፡፡ ይህ ለምን አሰፈለገ? አያት-ቅድመ አያቶቹ የሞቱላትን የኢትዮጵያ ባንዲራ ኦነግና ወያኔ ሲወጓት ኖረዋል፤ አይበቃቸውም? መቸ ነው ከኢትዮጵያ ጠላትነት ተመልሰው ለዜጎች የጋራ አገር ግንባታ የሚቆሙት?
የኦሮሞ ቄሮወች፥ የጠባብ ዘረኛውና የፀረ ኢትዮጵያው ኦነግ መሣሪያ እንደማይሆኑና ሁሉም በዕኩልነትና በነፃነት ተከብሮ ለሚኖርባት ኢትዮጵያ የተጀመረውን ትግል እምደሚቀጥሉ የሕዝብ እምነት ነው፤ የቄሮ ትግል ሌላ፡ የኦነግ ትግል ግንጠላ፤ ወጣቱ ከስሜታዊነትና ራሱ ፈራጅና እርምጃ ወሳጅ ከመሆን መራቅ አለበት፤ ሥርዓተ አልበኝነትን መከላከልና ሰከን ብሎ ማሰብና ማመዛዘን ያስፈል፤ ከፀረ ሰላሞች መጠንቀቅና ማስተዋል ይገባል፤ ሁሉን በጉልበትና በኃይል አስገድዶ ለማስፈጸም መሞከር ወደ እርስ በርስ እልቂትና ወደአለፈው አረመኔ አገዛዝ እንዳይመልሰን ያሰጋል፡፡ ሁሉም በጉልበት የፈለግሁትን ላድርግ ካለ መተላከቅ ስለሚፈጠር መንግሥት ወደኃይል እርምጃ እንዲመለስ ግድ ይሆናል፤ መብት ከግዴታ ጋር ከልተዋሀደ የጨለማ ጉዞ ነው የሚሆነው፤ ይህንን ለውጥ መንከባከብ ይገባል፡፡ «ውሻ በቀደደው ጅብ ይገባል»የሚባለው እንዳይሆን አርቆ ማሰብ እጅግ ያስፈልጋል፡፡