▽ Subscribe Youtube channel Ethiopa Tube to watch the news every day
➞ Youtube : abbaymedia.info

2 COMMENTS

  1. ዲሠምበር 25፣2017
    የተጠመደው
    መግቢያ፡ ከውጭ ስታዩት በጣም ደስ የሚል፣ ነገር ግን መንፈሳችሁ የሚያስጠነቅቃችሁ ነገር አይታችሁ ታውቃላችሁ?
    ከሠወሩብኝ ወጥመድ፣ ዓመፅንም ከሚያደርጉ ሠዎች ዕንቅፋት ጠብቀኝ። እኔ ብቻዬን እስካልፍ ድረስ ኃጢአተኞች በወጥመዳቸው ይውደቁ። መዝ 141፥9
    በጣም ቀላልና ውጤታማ የሆነውና ለዓመታት ስንጠቀምበት የነበረው የወጥመድ አይነት የጉድጓድ ወጥመድ ነው። አዳኞች ጥልቅ ጉድጓድ ይቆፍራሉ፣ በጉድጓዱ ወለል ላይም የሾሉ እንጨቶች ይረበርባሉ። ጉድጓዱን በቅጠላ ቅጠል ከሸፈኑ በኃላ በጉድጓዱ መሀል ላይ ተጠማጁን የሚስብ አጓጊ የሆነ ነገር ያስቀምጣሉ። ተጠማጁም የማጥመጃውን ምግብ ለመብላት ሲሄድ ወደ ጉድጓዱ ይወድቃል፣ በወጥመዱም ይያዛል። በጣም ጥሩ ይመስል የነበረው ነገር፣ በጣም መጥፎ ወደ ሆነ ነገር ተቀይሮ ይገኛል።
    እኛም በክርስቲያናዊ ህይወታችን ተግተን ሳለን፣ ጠላታችን የምንወድቅበትን ጉድጓድ በመቆፈር ይተጋል። አጓጊ የሆኑ አደጋዎችን ከፊታችን ይደቅናል፣ በዚህም እኛ ከተሳብን ውድቀታችንን በዓለም ሁሉ በማወጅ ለዓለም አሳልፎ ይሰጠናል።
    በዓለም የተሣቀባቸው የወደቁ ክርስቲያኖች የዲያብሎስ የደስታ ምንጭ ናቸው። የፈረሱ ቤቶች፣ የተሠበሩ ሠዎች፣ እና የተለያዩ ሱሶች የሚጀምሩት በቀላሉ ነው። ሠዎች ሲወድቁ በውስብስብ የወጥመድ ቀለበት ውስጥ ይገቡና ለመውጣት በጣም ይቸገራሉ።
    የህይወታችሁን ጤነኛ ሚዛን ጠብቁ። ከመንፈስ ቅዱስ ትንሽ ማስጠንቀቂያ ስታገኙ ከዛ ክፉ ነገር ሽሹ። እግዚአብሔር ወደ ወጥመድ ያስገባችኃልን? በእርግጥ ወደ ወጥመዱ የምንገባው የእግዚአብሔርን ሳይሆን የራሳችንን ፍላጎት በመከተል ነው። ዓሣ ወደ ማጥመጃ ምግቡ የሚሄደው በራሱ ውስጥ ያለው ፍላጎት ገፋፍቶት ነው። ለዛ የማጥመጃ ምግብ ፍላጎት ከሌለው በወጥመዱ አይያዝም።
    ዳዊት ከጠላቶቹ ወጥመድ ያመልጥ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ፀለየ (መዝ 141፥9)። እየሱስ ክርስቶስ በዋናው ፀሎት እንዲህ ብሎ ነገረን ፟ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን ፟ ማቴ 6፥13። ከአጓጊ አደጋዎች መንገዳችሁን ጠብቁ፣ ከወደቃችሁም እግዚአብሔር ከውድቀታችሁ እንደሚያነሳችሁ እወቁ። አሁንም አልረፈደም።
    ፀሎት፡ ሠማያዊ አባቴ ሆይ በጠላቶቼ ወጥመድ ውስጥ እንዳልወድቅ እርዳኝ። የተዘረጋልኝን ወጥመድ በቀላሉ እንዳየውና ከመንገዴ እንዲወገድ እርዳኝ። አፅናኙን መንፈስ ቅዱስ እንደቃልህ ላክልኝ፣ በሠላምህ፣ በፍቅርህ እና በፀጋህ ሸፍነኝ። በጌታ በእየሱስ ክርስቶስ ሥም ፀለይኩኝ አሜን።
    ከሪፍሬሺንግ ሆፕ ሚኒስትሪ የተወሰደ
    በ ፓስተር ዲዬን ቶድ የቀረበ

  2. ዲሠምበር 16፣2017
    ግማሽ ባዶ ብርጭቆ
    መግቢያ፡ ማዕዳችሁ የሞላላችሁ ወይም በትከሻችሁ የተሸከማችሁት ሸክም የከበዳችሁ መስሎ ከተሰማችሁ የዛሬውን መልዕክት አንብቡ።
    ገርነታችሁ ለሠው ሁሉ ይታወቅ። ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በፀሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሠላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ እየሱስ ይጠብቃል። በቀረውስ ወንድሞች ሆይ እውነተኛ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ጭምትነት ያለበትን ነገር ሁሉ፣ ፅድቅ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ንፁህ የሆነውን ነገር ሁሉ፣ ፍቅር ያለበትን ነገር ሁሉ፣ መልካም ወሬ ያለበትን ነገር ሁሉ፣ በጎነት ቢሆን፣ ምስጋናም ቢሆን፣ እነዚህን አስቡ ከእኔ የተማራችሁትንና የተቀበላችሁትን፣ የሠማችሁትንም ያያችሁትንም እነዚህን አድርጉ የሠላምም አምላክ ከእናንተ ጋር ይሆናል። ፊሊ 4፥5
    በአንድ ምግብ ቤት ጠረጴዛ ላይ በብርጭቆ የተቀመጠን ውሃ አስቡ። ለአንድ ሠው ብርጭቆው ግማሽ ብርጭቆ ውሃ የያዘ ለሌላው ሠው ደግሞ ግማሽ ባዶ ሆኖ ሊታይ ይችላል። በማንኛውም መልኩ ብታዩት ብርጭቆው የያዘው አንድ አይነት መጠን ነው።
    ህይወታችሁን በሠይጣን እይታና እቅድ መሠረት ከተመለከታችሁት ጨለማ፣ ጠመዝማዛና፣ የጨፈገገ እይታና በመጠራጠር፣ በጉድለት፣ በተስፋ መቁረጥ፣ በብቸኝነትና በፍርሃት እንድትሞሉ ያደርጋችኃል። ብርጭቆውም በውስጡ ያለው ውሃ ፈፅሞ እስኪያልቅ መጉደሉ አይቀሬ ነው። ከዛ ምን ታደርጋላችሁ?
    ህይወታችሁን በእየሱስ እይታና እቅድ መሠረት ከተመለከታችሁት ተስፋ፣ ፍቅር፣ ብርሃን፣ ተቀባይነት፣ ይቅር ባይነት የተሞላ መሆኑንና ምንም ነገር ቢመጣ እግዚአብሔር አብሮዋችሁ መሆኑን አውቃችሁ ቀናችሁን ትቀበላላችሁ። በብርጭቆው ውስጥ ያለው ውሃ ቢያልቅ አስተናጋጁ በድጋሚ እንደሚሞላላችሁ እርግጠኛ ናችሁ። ፟ኃይልን በሚሠጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፟ ፊሊ 4፥13። ፟በአንቺ ላይ የተሰራ መሣሪያ ሁሉ አይከናወንም ፟ ኢሣ 54፥17። ስለዚህም በድፍረት እንዲህ ማለት እንችላለን ፟ጌታ ይረዳኛልና አልፈራም፣ ሠው ምን ያደርገኛል? ፟ ዕብ 13፥6።
    ህይወታችሁን ከማን አቅጣጫ እየተመለከታችሁ ነው? አለምን በትከሻችሁ ተሸክማችሁ የምትዞሩ ያህል ሆኖ ከተሠማችሁ ይህ ትክክል ያልሆነውና በዛሬው ጊዜ የተለመደው እይታ ነው። ህይወት ውጥረት ነው፣ በብዙ አቅጣጫ የሚጎትቱን ብዙ ነገሮች ይኖራሉ። ይህን አይነት ሁኔታ በህይወታችሁ እንዲከሠት አትፍቀዱ። ሁል ጊዜ ለሁሉም ሠው ሁሉንም ነገር እንድትሆኑ አይጠበቅባችሁም። ራሳችሁን ሁኑ፣ ሊቀበሉዋችሁም ላይቀበሉዋችሁም ይችላሉ፣ ይህ መልካም ነው። እግዚአብሔር ግን በትክክል ይቀበላችኃል።
    ጳውሎስ እንደፃፈው ፟ስለምንም ነገር አትጨነቁ፣ በትጋት ፀልዩ፣ እናም ጥያቄዎቻችሁን ለእግዚአብሔር አሳውቁ ፟ ምክንያቱም የሠላም አምላክ የሚመጣው የዚህን ጊዜ ነውና። እየሱስ ክርስቶስ በማቴዎስ ወንጌል 6፥34 እንዲህ ብሎአል ፟ነገ ለራሱ ይጨነቃልና ለነገ አትጨነቁ ለቀኑ ክፋቱ ይበቃዋል። ፟
    ጳውሎስ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ ይበቃኛል የሚለውን ትምህርት በፊሊ 4፥11 ላይ አስተምሮናል፣ ፟ይህን ስል ስለጉድለት አልልም፣ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም፣ መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። ኃይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ። ፟
    ስለዚህ ዛሬም አትጨነቁ ተስፋም አትቁረጡ። የጠፋው ይተካል፣ የተሰረቀው ይገኛል፣ እግዚአብሔር ስላደረገላችሁ ነገር በፀሎት አመስግኑ። በህይወታችሁ ውስጥ የሰራበትን ጊዜ አስቡ። ህይወታችሁን ህይወቱን በመስቀል ላይ አሳልፎ እስከመስጠት ድረስ በሚወዳችሁ በእየሱስ ክርስቶስ መንገድ አድርጉ። እግዚአብሔር ማንንም አይጥልም።
    ፀሎት፡ የሠማይ አባታችን ሆይ፣ ለዛሬዋ እለት ስላደረስከኝ አመሰግንኃለው። ምን ላደርግልህ እንደምትወድ ንገረኝ። የተገለጠ ራዕይ ስጠኝ፣ የአምሮ ሠላም ስጠኝ፣ በህይወቴ ሠላምህን አብዛልኝ፣ እንድለወጥና አንተን እንድመስል ፀጋህን አብዛልኝ። በእየሱስ ክርስቶስ ሥም ፀለይኩኝ አሜን።
    ከሪፍሬሺንግ ሆፕ ሚኒስትሪ የተወሰደ
    በ ፓስተር ዲዬን ቶድ የቀረበ

LEAVE A REPLY