50 COMMENTS

  1. ውድ የተዋህዶ ልጆች ኪዳነ ምህረት የልባችንን መሻት ትፈፃምልን
    አሜን
    አሜን
    አሜን

  2. ✔ ለምንድን ነው የምንጾመው? ✔

    እንደ አንድ ክርስቲያን [በግልም በአዋጅም] በመደበኛነት እንድንጾም ታዝዘናል፡፡ ኾኖም እስኪ ጥያቄ እናንሣ! ለምንድን ነው የምንጾመው? በመራባችን ምክንያት እግዚአብሔር ደስ ይሰኛልን? በየቀኑ እግዚአ ብሔርን ለማገልገል በቂ ነው የሚባል ምግብ ልናገኝ እንደሚገባን የታ ወቀ የተረዳ ነው፡፡ ታዲያ በዚህ [በመጾማችን – በመራባችን] ውስጥ ያለው ምሥጢርና እግዚአብሔር ከዚያ ውስጥ የሚፈልግብን ፍሬ ምንድን ነው?

    በልብ መታሰቡ፣ በቃል መነገሩ፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም መዘከሩ ይክበር ይመስገንና ጌታችንና መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስም በመጾ ማቸው ምክንያት የሚገበዙትን እጅግ ወቅሷቸዋል፡፡ ጾም የሚያስታብይ አይደለም ሲላቸው ነው፡፡
    ስለዚህ እግዚአብሔር እንድንጾም የሚፈልገው ስለ ኹለት ዋና ዋና ምክንያቶች ነው፡-

    #አንደኛው፥ ራሳችንን ከዚህ ዓለም ነገሮች – ከእነርሱ ዋናውም ከምግብ – አርቀን ወደ መንፈሳዊ ነገሮች እንድናቀርብ ስለሚፈልግ ነው፡፡ በየጊዜው በየሰዓቱ ስንበላ ሥጋችን ተድላ ደስታ ያደርጋልና፡፡ በመሠረቱ ምግብ በልቶ ደስ መሰኘት በራሱ ነውር ኾኖ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር የአማናዊ ተድላና ደስታ ምንጩ መንፈሳዊ ተግባር እንደ ኾነ እናስብ ዘንድ ይሻል፡፡ ስለዚህ እንድንጾም የሚፈልገ ውና በዚያውም ውስጥ እንድናስተውለው የሚፈልገው የመጀመሪያው ምክንያት ይኸው ነው፡፡

    #ኹለተኛው ምክንያት ደግሞ ማጣት ዘወትር እንዲራቡ ከሚያደርጋቸ ው ሰዎች ጋር አንድነትና ኅብረት እንዲኖረን ስለሚሻ ነው፡፡ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያንን ተከትለን በየጊዜው ልንጾም እንችላለን፡፡ ይህ ሥርዓተ ቤተ ክርስቲያን አስገድዶአቸው ሳይኾን እጦት አስገድዶአቸው ያለማቋ ረጥ ዘወትር የሚጾሙ ሰዎች ግን አሉ፡፡ እግዚአብሔር ደግሞ ለእነዚህ ሰዎች እውነተኛ ፍቅር እንድናሳይ ይፈልጋል፡፡ አጥቶ የመራብ ትር ጕሙ ምን ማለት እንደ ኾነ እኛው ራሳችን በተግባር እንድናይ ይሻል፡፡ በጾማችን ውስጥ እንድናፈራው የሚፈልገው አንዱ ፍሬ ይኼ ነው፡፡ ጾም የፍቅረ ቢጽ እናት ነች የምንለውም ለዚህ ነው፡፡

    ስለዚህ ጾማችን እግዚአብሔር የሚፈልገውና የሚቀበለው እንዲኾንልን በጾማችን ወቅት ወጪአችንን መቆጠብ ሳይኾን እነዚህን ድኾች እንድ ናስብ ያስፈልጋል፡፡

    © አምስቱ የንስሐ መንገዶች፣ በቅዱስ ዮሐንስ አፈወርቅ፣ ገጽ 71-72

LEAVE A REPLY